ምክር ቤቱ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያል

104

ሰኔ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በሚያካሂደው 16ኛ መደበኛ ጉባዔ ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በወቅታዊ ጉዳዮች ይወያያል።

በዚህ መደበኛ ጉባዔው፤ ሰሞኑን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ላለው የዜጎች የፀጥታ እና ደኅንነት ጉዳይ ዋነኛ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ ይጠበቃል።

እንደዚሁም ለሌሎች ማኅበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ምጣኔ-ሀብታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ትኩረት ተሰጥቶ፤ ምክር ቤታዊ ውይይት ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም፤በአዲሱ የ2015 የበጀት ድልድል ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቀው፣ ለዕለቱ የተያዘው የአጀንዳ መረጃ ያመላክታል።

በተያያዘ ዜናም፤ የፌዴራል መንግስት አጠቃላይ ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትም የሚቀርብ ሲሆን፣ በዚሁ ሪፖርት ላይም ምክር ቤቱ ከጠቅላይ ሚኒሰትሩ ጋር እንደሚወያይ ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም