"ክብር ለጥበብ" አገር አቀፍ የእውቅና እና የሽልማት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

210

ሰኔ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) "ክብር ለጥበብ" የተሰኘው ሁለተኛው አገር አቀፍ የእውቅና እና የሽልማት መርሃ ግብር ማምሻውን በሸራተን አዲስ ሆቴል በመካሄድ ላይ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ አንጋፋና ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል፡፡

መርሃ ግብሩ የተዘጋጀው በ10 የተለያዩ የጥበብ ዘርፎች በመሰማራት አስተዋጽኦ ላበረከቱ፣ ለኢትዮጵያ የባህልና የልማት እንቅስቃሴ እድገት አስተዋጽኦ አድርገዋል ለተባሉ ከ40 በላይ ለሚሆኑ አንጋፋና ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች እውቅና ሽልማት ለመስጠት ነው።

ሙዚቃ፣ ጽሁፍ፣ ፋሽን፣ ዕደ ጥበብ ዲዛይን፣ ሲኒማ እና ቴአትር ከተዘጋጁት ዘርፎች መካከል ይገኙበታል።

የመጀመሪያው የእውቅናና የሽልማት መርሃ-ግብር በ2013 ዓ.ም ”ሽልማት ለጥበብ” በሚል መሪ ቃል መካሄዱ ይታወሳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ፤

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም