የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ከ650 ሺህ በላይ ለሆኑ ወገኖች የምግብ እርዳታ እያደረገ መሆኑን ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ከ650 ሺህ በላይ ለሆኑ ወገኖች የምግብ እርዳታ እያደረገ መሆኑን ገለጸ
99
ሰኔ 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) የዓለም ምግብ ፕሮግራም በአፋር ክልል ከ650 ሺህ በላይ ለሆኑ ወገኖች የምግብ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን አስታወቀ።
የድርጅቱን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በሰሜናዊ አፋር ኮኔባ አካባቢ ዛሬ መድረሳቸውንና ወደ መጋዘን እየተራገፈ እንደሚገኝ አመልክቷል።
በየስድስት ሳምንት ልዩነት “በአፋር ክልል በግጭትና በድርቅ ምክንያት” ለተፈናቀሉ ከ650 ሺህ በላይ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ጠቁሟል።
የዓለም ምግብ ፕሮግራም ባለፈው ሳምንት በክልሉ ለ80 ሺህ ዜጎች የሚሆን የምግብ እርዳታ ማድረሱንና የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ገልጿል።
በአፋር ክልል በጦርነቱ ምክንያት 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የክልሉ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት መረጃ ያሳያል።