በአዲስ አበባ 25 ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በነገው እለት ለነዋሪዎች በዕጣ ይተላለፋሉ

208

ሰኔ 29/2014/ኢዜአ/ በአዲስ አበባ 25 ሺህ 491 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በነገው እለት ለነዋሪዎች በዕጣ ይተላለፋሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፤ በነገው እለት የሚካሄደውን የ3ኛ ዙር የ40/60 እና 14ኛ ዙር የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

ከንቲባዋ በመግለጫቸው በ20/80 ፕሮግራም 18 ሺህ 648 እንዲሁም በ40/60 መርኃ ግብር 6 ሺህ 843 ቤቶች በድምሩ 25 ሺህ 491 ቤቶች ለነዋሪዎች በእጣ ይተላለፋሉ ብለዋል።

በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም አያት 2፣ ቦሌ በሻሌ፣ ቡልቡላ ሎት ሲሆኑ በ20/80 በረከት፣ ቦሌ አራብሳ ሳይት 3 ሳይት 5 እና 6 ወታደር፣ የካ ጣፎ፣ ጀሞ ጋራ፣ ጎሮ ስላሴ ፣ ፉሪ ሀና እና ፋኑኤል ናቸው።

የመንግስት ሰራተኛ 20 በመቶ፣ ሴቶች 30 በመቶ፣ የአካል ጉዳተኞች 5 በመቶ በእጣው ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም