የአምቦ ዩኒቨርሲቲ 3 ሺህ 921 ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል

215

አምቦ፣ ሰኔ 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአምቦ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 921 ተማሪዎች ነገ ያስመርቃል።

የዩኒቨርሲቲው ሪጅስትራር ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር ዶክተር ገዳ ከበደ ለኢዜአ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው በነገው እለት ከሚያስመርቃቸው ተማሪዎች መካከል 906ቱ ሴቶች ናቸው።

ተመራቂዎች በመደበኛና ተከታታይ መርሀ ግብር በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ ዲግሪ ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ መሆናቸውን ተናግረዋል ።

"በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት በዩኒቨርሲቲው ተመድበው ትምህርታቸውን የተከታተሉ 448 ተማሪዎችም በዕለቱ ይመረቃሉ" ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲው አመራሮችና መምህራን፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት የምረቃ ስነ ስርአቱን ለማካሄድ ዝግጅት መደረጉን ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም