ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሃ ግብር አስጀመሩ

94

አዲስ አበባ ሰኔ 24/2014 /ኢዜአ/ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሃ ግብር አስጀመሩ ።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ወረዳ 2 ሃምሌ 19 አከባቢ የአቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ መርሃ ግብር ጀመረ ።

የቤት እደሳ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ናቸው ።

በዚሁ ወቅት እንዳሉትም በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን ህይወት ማሻሻል የመንግስት ዋነኛው ትኩረት ነው ብለዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴርም በመጀመሪያው ዙር በጉለሌ ክፍለ ከተማ 12 ቤቶችን እንደሚያድስም ተገልጿል።

ለዚህም 5 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር መመደቡም ተገልጿል።

የቤት ዕድሳት የተጀመረላቸው ነዋሪዎችም የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም