ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጡ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጡ
184
ሰኔ 23 ቀን 2014 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሚኒስትሩ በመንግስት በኩል ሰላም ለማምጣት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች፣ በኢትዮጵያና ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ የአገራዊ ምክክር ዝግጅትና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ ገለጻ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።