የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ወይዘሮ ዛህራ ሑመድን የሊጉ ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጠ

228

ሀዋሳ፣ ሰኔ 23 ቀን 2014(ኢዜአ) በሃዋሳ ከተማ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ እየተካሄደ ያለው የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አንደኛ ጉባኤ ወይዘሮ ዛህራ ሑመድን የሊጉ ፕሬዝዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ መርጧል።

ወይዘሮ ዛህራ ሑመድ የብልጽግና ፓርቲ የሴቶች ሊግን በፕሬዝዳንት እንዲያገለግሉ በጉባኤው የተመረጡት 713 ድምፅ አግኝተው ነው።

እንዲሁም ወይዘሮ መስከረም አበበና ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን 553 እና 486 ድምፅ በቅደም ተከተል በማግኘት የሊጉ ምክትል ፕሬዝዳንቶች ሆነው በጉባኤው ተመርጠዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አንደኛ ጉባኤ የቀጠለ ሲሆን የሊጉን የሥራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽነሮችን እንደሚመርጥ ይጠበቃል ሲል የኢዜአ ሪፖርተር ከስፍራው ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም