ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ ባለ 5 ወለል ህንጻ የመኖሪያ ቤት ግንባታን አስጀመሩ

146

ሰኔ 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ ባለ 5 ወለል ህንጻ የመኖሪያ ቤት ግንባታን አስጀመሩ።

በዚሁ ስነስርዓት ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደተናገሩት በዚህ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ የህዝቡን ተስፋ ለማለምለም፤ በኑሮ ውድነትና በቤት እጦት የሚሰቃየውን ህዝብ በምንችለው ለማገዝ ጥረት እያደረግን ነው፡፡

ጌጃ ወይም ከረዩ ሰፈር ብዙ ጉስቁልና የነበረበት ሲሆን ጠጋ ብለን ተመልክተን መመለስ ብቻ ትክክል አይሆንም ያሉት ከንቲባ አዳነች ማድረግ የምንችለውን ነገር ሁላችን ስናደርግ ህዝባችን ተስፋው ይለመልማል፤ጠንክሮም ይሰራል ብለዋል፡፡

የልደታ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ሀ/ጊዮርጊስ በበኩላቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን ነድፈን እየሰራን ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች በልደታ ክ/ከተማ በ60 ቀናት የጓሮ አትክልት ልማት ስራዎች የደረሱ አትክልቶችን ለአካባቢው ማህበረሰብ የማእድ ማጋራታቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡