በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር የተከበረው የዘመን መለወጫ በዓል የሰላምን ፋይዳ በተግባር ያረጋገጠ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ

90
አዲሰ አበባ  መስከረም 1/2011 በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር የሁለቱ አገሮች ህዝቦችና የሰራዊት አባላት በተገኙበት ዛሬ የተከበረው የዘመን መለወጫ በዓል የሰላምን ፋይዳ ከንግግር በላይ በተግባር ያረጋገጠ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበዓሉ ላይ ከታደሙ በኋላ ዛሬ ከቀትር በኋላ አዲስ አበባ ሲመለሱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ ''ክስተቱ የሁለቱን አገሮች ህዝቦች ፍላጎት ያሳካና የሰላምን ኃያልነት በተግባር ያንፀባረቀ መሆኑን መገንዘብ የተቻለበት ነው'' ብለዋል። ክንዋኔው የሁለቱ አገሮች ሰንደቅ ዓላማዎች በጋራ መሳ ለመሳ የተውለበለበበት እጅግ ያማረ ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ህጻናት፣ አረጋዊያን፣ ወታደሮች በተፈጠረው አጋጣሚ ምን ያህል እንዳነቡ ስናይ፤ የሰው ልጅ በመጠላላት ለምን ወደጦርነት ይገባል የሚል ጥያቄ እንዲነሳ ያደርጋል፤" ብለዋል። በበዓል አከባበሩ ላይ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ተገኝተዋል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም