ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቻይናው ፕሬዝዳንት በተዘጋጀው የብሪክስ ፕላስ የከፍተኛ አመራሮች ዓለም አቀፍ የልማት ውይይት ላይ ተሳተፉ

98

ሰኔ 17 ቀን 2014 (ኢዜአ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በተዘጋጀው የብሪክስ ፕላስ የከፍተኛ አመራሮች ዓለም አቀፍ የልማት ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።

''በልማት ውይይቱ ላይ በመሳተፌ ደስ ብሎኛል ያሉት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደነዚህ ያሉት መድረኮች የጋራ ትግበራ ሲታከልባቸው፣ እንደ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የተጋፈጥናቸውን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች ለመፍታት ትልቅ አስተዋፅዖ ያደርጋሉ'' ብለዋል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም