በደምቢዶሎ ዶክተር አብይ አህመድን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

64
ጊምቢ ግንቦት 10/2010 ደምቢዶሎን እንደሚጎበኙ የሚጠበቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ለመቀበል ዝግጅት መደረጉን የቄለም ወለጋ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ  አቶ ስንታየሁ ተረፈ እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች  ከነገ በስቲያ ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ እንደሚመርቁና የደምቢዶሎ አውሮፕላን ማረፊያን በረራ እንደሚያስጀምሩ ይጠበቃል። ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አቀባበል ለማደረግም አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት መደረጉን  አስታውቀዋል፡፡ ዶክተር አብይ አህመድ  ከዞኑ ከተወከሉ የህብረተሰብ ክፍሎችና ከደምቢዶሎ ከተማ ነዋሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደምቢዶሎን የሚጎበኙ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ በስፍራው የሚገኘው ሪፖርተራችን ዘግቧል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም