በአፋር ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ- ግብር እየተካሄደ ነዉ

195

ሰመራ፣ ሰኔ 14 ቀን 2014 /ኢዜአ/ በአፋር ክልል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ- ግብር እየተካሄደ ነዉ::

በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳፉ ይገኛሉ::

በክልል ደረጃ 14 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል እቅድ የተያዘ ሲሆን የዛሬዉ መርሃ ግብርም የዚሁ እቅድ አካል መሆኑም ታውቋል::

በዚህ ክረምት ከ4ሚሊዮን በላይ ችግኝ የሚተከል ሲሆን ቀሪዉ 10ሚሊዮን ደግሞ ከመስከረም በኋላ በክልሉ ለችግኝ ተከላዉ ተስማሚ በሆነ የአየር ንብረት ወቅት እንደሚተከል ተመልክቷል ::

የችግኝ ተከላዉ በሁሉም የክልሉ አስተዳደር እርከኖች አየተከናወነ ሲሆን በዛሬዉ ቀንም ከ1ሚሊዮን በላይ ችግኝ እንደሚተከልም ይጠበቃል::

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም