በኢትዮጵያ በአራት አመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል እቅድ ዘንድሮ ይሳካል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ - ኢዜአ አማርኛ
በኢትዮጵያ በአራት አመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል እቅድ ዘንድሮ ይሳካል -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
95
ሰኔ 12 ቀን 2014 (ኢዜአ)በኢትዮጵያ በአራት አመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል እቅድ ዘንድሮ እንደሚሳካ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት በዘንድሮው ክረምት በአረንጓዴ አሻራው 6 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት ተደርጓል።
የአረንጓዴ አሻራውም ሰኔ 14 ቀን እንደሚጀመር የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመርሃ ግብሩም 7 ነጥብ 2 ቢሊዮን ችግኞች ተዘጋጅተዋል ነው ያሉት።