የኦዲ ቦኮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት እየተመረቀ ነው

147

ሀዋሳ፣ ሰኔ 11 ቀን 2014 (ኢዜአ) የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በሲዳማ ክልል ሆኮ ወረዳ ያስገነባዉ ኦዲ ቦኮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምረቃ ሥነ-ሥርዐት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

በምርቃት ሥነ-ሥርዐቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ እንዲሁም የተለያዩ ሀላፊዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም