መደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

187

ጎባ፤ ሰኔ 11/2014 (ኢዜአ) መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን 932 ተማሪዎችን እያሰመረቀ ነው።

ከተመራቂዎች መካከል 234 የሚሆኑት ሴት ተመራቂዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ በኢንጂነሪንግ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ፣ በጤና ሳይንስና  በሌሎች የትምህርት  መስኮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በምረቃው መርሐ ግብር የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ፕሮፌሰር በላይ ሲመኔን  ጨምሮ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አህመድ ከሊልና ሌሎች የቦርድ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በ1999 ዓ.ም የመማር ማስተማሩን ስራ የጀመረው የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት ከ20 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን በተለያዩ መርሐ ግብሮች እያስተማር እንደሚገኝ ከዩኒቨርሲቲው የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም