የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ405 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ

214

ሰኔ 10/2014 (ኢዜአ)  የገንዘብ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር የ405 ሚሊዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ከዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ተወካይ ኦስማን ዲዬ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

ገንዘቡ ለበአርብቶ አደርና ደረቃማ አካባቢ የከርሰ ምድር ውሃ ልማት እንዲሁም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመካከል እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡

በዚህም 210 ሚሊዮን ዶላሩ በአርብቶ አደርና ደረቃማ አካባቢ የከርሰ ምድር ውሃ ልማት የሚውል ሲሆን ቀሪው ደግሞ የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ይውላል ነው የተባለው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም