የሳንሱሲ -ታጠቅ-ኬላ መንገድ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
የሳንሱሲ -ታጠቅ-ኬላ መንገድ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነ
78
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2014(ኢዜአ) የሳንሱሲ -ታጠቅ-ኬላ መንገድ ግንባታ ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አስታወቀ፡፡
መንገዱ ከ13 ነጥብ 5 በላይ ኪሎ ሜትር የሚረዝም ሲሆን ግንባታውን ያከናወነው አሴር አገር በቀል ግንባታ ተቋራጭ ነው፡፡
ለመንገዱ ግንባታ ከ825 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ታውቋል፡፡
መንገዱ እስከ 32 ሜትር ድረስ የጎን ስፋት ያለው ሲሆን በግራና በቀኝ 6 ተሽከርካሪዎች ማስተናገድ የሚችል ነው፡፡
በዛሬው እለትም የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር አመራሮች የመንገዱን አጠቃላይ ሁኔታ ጎብኝተዋል፡፡