ምክር ቤቶቹ የጋራ በሚያደርጓቸው አገራዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

63

ሰኔ 10/2014/ኢዜአ/ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የጋራ በሚያደርጓቸው አገራዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሔል ባፌና የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሔኖክ መለሰ ተፈራርመዋል፡፡

በስምምነቱ መሰረትም ምክር ቤቶቹ በአገራዊ ምክክሩ፣ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ ግጭት አፈታትና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ የሚሰሩ ይሆናል፡፡

በተለይም አገራዊ የምክክር ሂደቱ የተሣካ እንዲሆን ምክርቤቶቹ በጋራ በመስራት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት የሚወጡ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

የሁለቱ ምክር ቤቶች በትብብር መስራት አገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ህዝብን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ሚናው የጎላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም