ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ወላይታ ሶዶ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ወላይታ ሶዶ ገቡ
157
ሶዶ፣ ሰኔ 10/2014 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ወላይታ ሶዶ ገቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩና ቀዳማዊት እመቤት ወላይታ ሶዶ ከተማ ሲደርሱ በአካባቢው ነዋሪዎችና አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩና ቀዳማዊት እመቤት በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከአንድ ዓመት በፊት ግንባታው የተጀመረው የዳቦ ፋብሪካና ሌሎች የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ ተገልጿል።
በቆይታቸው ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።