'በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር' የአዲስ አመት ማብሰሪያ መርሃ-ግብር ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይታደማሉ

62
አዲስ አበባ ጳጉሜ 5/2010 'በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር' በሚል ዛሬ ምሽት በሚካሄደው አዲስ ዘመን ማብሰሪያ መርሃ-ግብር ላይ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚያን በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ተገኝተዋል። አሮጌውን ዓመት በመሸኘት አዲሱን ለመቀበል መንግስት ባዘጋጀው በዚህ መርሃ-ግብር ላይ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል መንግስታት ባለስልጣናትን ጨምሮ የኃይማኖት አባቶች ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት እንዲሁም ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ዜጎች የዝግጅቱ ታዳሚያን ሆነዋል። በምሽቱ ክንዋኔ የተለያዩ የድንገቴ መርሃ-ግብሮች እንደሚኖሩ የሚጠበቅ ሲሆን ኢትዮጵያውያን በሰላም፣ በፍቅርና በይቅርታ ተደምረው  ለአንድነት እንዲተጉ የሚያነሳሱ መልዕክቶችን ያዘሉ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም