የአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ 1 ሺህ 900 መፃህፍት ለአብርሆት ቤተመፃህፍት አስረከበ

116

ሰኔ 1 ቀን 2014 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር ካሉ ሰራተኞቹ ያሰባሰባቸውን 1 ሺህ 900 መፃህፍት ለአብርሆት ቤተመፃህፍት አስረከበ።

ቢሮው የስነፅሁፍ፣የህግ፣የኮሙዩኒኬሽን፣ታሪክና የተለያዩ ይዘት ያላቸውና በአገር ውስጥና በውጭ ፀሀፊያን የተፃፉ መፃህፍትን ነው ለቤተመጻህፍቱ በዛሬው እለት ያስረከበው።

የቢሮው ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት ቢሮው ከዚህ ቀደም ሌሎች ተቋማት መፃህፍት እንዲያበረክቱ ሲያስተባብር ቆይቷል።

በዛሬው እለት ቢሮው ከማዕከል ጀምሮ እስከ ወረዳ ባለው መዋቅር ካሉ ሰራተኞች ያሰባሰባቸውን 1 ሺህ 900 መፃህፍት ዛሬ ማስረከቡንና በቀጣይም ድጋፉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

መፃህፍቱን የተረከቡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተወካይ ዶክተር ታምራት ሀይሉ በበኩላቸው ቢሮው እየተካሄደ ባለው የአንድ ወር የመፃህፍት አሰባሳቢ ንቅናቄ የብሄራዊ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል በመሆን ሲያስተባብር ቆይቷል።

በዛሬው እለት ላደረገው አበርክቶም ምስጋና አቅርበዋል።

ሚሊዮን መፃህፍት ለሚሊኒየሙ ትውልድ በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ተቋማት ለአብርሆት ቤተመፃህፍት መፃህፍትን እያስረከቡ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም