ኢዜአ በ2ኛ ዙር ያሰባሰባቸውን 2ሺህ መጻሕፍት ለአብሮሆት ቤተመጻሕፍት አስረከ

6

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 29 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) በ2ኛ ዙር ያሰባሰባቸውን 2 ሺህ መጻሐፍት ለአብሮሆት ቤተመጻሕፍት አስረከበ።

በአብርሆት ቤተ መፅሐፍት በተከናወነው የርክክብ ስነ-ስርአት ላይ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሰይፈ ደርቤ፤የጠቅላይ ሚንስትሩ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ ሙዓዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረትን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

መጻሕፍቱ የማህበራዊና የተፈጥሮ ሳይንስ ፤የቢዝነስ፣ የስነ-ጥበብ፣ የስነ-ፅሁፍና ኪነ-ጥበብ እንዲሁም የታሪክ ይዘት ያላቸው እንደሆኑ ተገልጿል።

መጻሕፍቶቹ ከዋናው መስሪያ ቤት ከሚገኙ ሰራተኞች እና ከክልል የኢዜአ ቅርንጫፍ ሰራተኞች የተሰበሰቡ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በአንደኛ ዙር ከ5 ሺህ በላይ መጻሕፍትን ማስረከቡ የሚታወስ ሲሆን በአጠቃላይ ለአብሮሆት ቤተ-መፅሐፍት ከ7ሺህ በላይ መፅሐፍትን አበርክቷል።