የጸጥታ ተቋማትን የምንገነባው ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ከሚፈልጉ ኃይሎች ለመከላከል ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

2

ግንቦት 28 ቀን 2014 (ኢዜአ) የጸጥታ ተቋማትን የምንገነባው ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ከሚፈልጉ ኃይሎች ለመከላከል ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “የምንገነባው ተቋማትን ነው” ብለዋል።

“የጸጥታ ተቋማትን የምንገነባው ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ከሚፈልጉ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለመከላከል ነው” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በኢትዮጵያ የተቋማት ግንባታ የሚካሄደው ኢትዮጵያን በሰላም ለማቆየት ብቻ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ተቋማቱ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና ለምታደርገው ሽግግር መሠረት ሆነው እንዲያገለግሉ ጠቅሰው፤ “ለልጆቻችን የበለጸገች ሰላማዊት ኢትዮጵያን እናወርሳለን” ብለዋል።