በሞጆ ከተማ አካባቢ ለውጭ ንግድ እየተዘጋጀ ያለው የአቮካዶ ችግኝ ጣቢያ ተጎበኘ

8

ግንቦት 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሞጆ ከተማ አካባቢ ለውጭ ንግድ እየተዘጋጀ ያለውን የአቮካዶ ችግኝ ጣቢያ እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈጉባኤ ሎሚ በዶና በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ ቤልጅጌን ጨምሮ የተለያዩ የቋሚ ኮሚቴ አባላትና አመራሮች ተገኝተዋል ።

በጉደቱ መስኖ ተጠቃሚዎች ህብረት ስራ ማህበር ከሄክታር በላይ በሆነ መሬት ላይ የሚለማው የተዳቀለ የአቮካዶ ችግኝ ለምርት በሚደርስበት ወቅት ለኤክስፖርት እንደሚውል ተመልክቷል ።

የክልሉ መንግስት የተሻሻሉና ለውጭ ንግድ የሚሆኑ የአቮካዶና ማንጎ ችግኞችን በክልሉ በርካታ አካባቢዎች እያዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል።