የኢትዮ-እስራኤል የንግድና ኢንቨስትመንት ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

118

ግንቦት 26 ቀን 2014 (ኢዜአ)  የኢትዮ-እስራኤል የንግድና ኢንቨስትመንት ምክክር በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮ-እስራኤል ንግድና ኢንቨስትመንትን ማሳደግ የሚያስችል የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ነው።

በምክክሩም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የፌደራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች፣ የንግድና የዘርፍ ማህበራት አመራሮች፣ በኢትጵያ የእስራኤል አምባሳደር አለሊ አድማሱ እና ሌሎች አካላትም በበይነመረብ እየተሳተፉ ይገኛል።

እየተካሄደ ያለው ምክክር የሁለቱን ሀገራት የቆየ ጥብቅ ዲፕሎማሲያዊ፣ ምጣኔ ኃብታዊ፣ ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ ግንኙነት ያጠናክራል ተብሏል።

በቀጣይም እስራኤል ያላትን የቴክኖሎጂ ልህቀት ተጠቅማ በኢትዮጵያ ያለውን ጸጋ በማልማት የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ምክክሩ እገዛ እንደሚያደርግም ተገልጿል።

የምክክር መድረኩን  ንግድና የዘርፋ ማህበራት እና የእስራኤል ኤምባሲ በመተባበር አዘጋጅተውታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም