ክለቡ የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አገኘ

74
መቀሌ ጳግሜ 4/2010 ወደ ፕሪሜር ሊግ መቀላለቀሉን ያረጋገጠው ስሑል ሽረ እንዳስላሴ እግር ኳስ የስፖርት ክለብ ከሱር ኮንስትራክሽን አክስዮን ማህበር  የ15 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አገኘ፡፡ ማህበሩ  በተጨማሪም ለክለቡ ተጫዋቾች በነብሰ ወከፍ  50ሺህ ብር  ለዋና አሰልጣኙ ደግሞ 75ሺህ ብር በሽልማት አበርክቷል፡፡ የተደረገው ድጋፍ አስር ሚሊዮን ብር  በጥሬ ገንዘብና ሲሆን  ቀሪው  ለትራንስፖርት የሚያገለግላቸው ዘመናዊ አውቶብስ መሆኑን የሱር ኮንስትራክሽን አክስዮን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ታደሰ የማነ ገልጸዋል፡፡ ለክለቡ  ድጋፉን የሰጡት ወደ ፕሪሜር ሊግ ከመቀላቀሉ በተጨማሪ በከፍተኛ ሊግ  ባደረጋቸው የእግር ኳስ ውድድሮች በሳየው ስፖርታዊ ጨዋነት   መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በርክክብ ስነ ስርዓቱ ወቅት የተገኙት የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ነጋ አሰፋ በበኩላቸው ሱር ኮንስትራክሽን  ላደረገው ድጋፍ  አመስግነው ይህም ለሌሎች አርአያ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዲህ እንዳለ  የትግራይ ጦር አካል ጉዳተኞች ማህበር በፕሪሜር ሊግ እየተሳተፉ ለሚገኙ አራት የክልሉ የእግር ኳስ ክለቦች በነብሰ ወከፍ 50ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል። ድጋፍ የተደረገላቸው የእግር ኳስ ክለቦች መቀሌ ከነማ፣ወልዋሎ አድግራት ዩኒቨርስቲ፣ደደቢትና ሰሞኑን ወደ ፕሪሜር ሊግ መቀላቀሉን ያረጋገጠው  ስሑል ሽሬ እንዳስላሴ የእግር ኳስ  ክለቦች ናቸው፡፡ ገንዘብ ድጋፉን የሰጡት የማህበሩ ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አጽበሀ አረጋዊ ናቸው፡፡ አቶ አፅበሃ  በዚህ ወቅት እንዳሉት  የክልሉን ስፖርት ለማሳደግ ማህበሩ ካለው ፍላጎት በመነሳት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡ የገንዘብ ድጋፉ የተረከቡ የክልሉ እግር ኳስ ፌዴረሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንገሶም ካህሳይ በበኩላቸው ድጋፉ ክለቦቹ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖራቸው  የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም