"ኢትዮጵያ የሰብዓዊ እርዳታ ለሚሹ ዜጎች ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ ናት" -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

91

ግንቦት 20 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በትዊተር ገጻቸው እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ለተጎዱ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ እንዲደርስ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸው፤ አጋሮች በመላው አህጉሪቱ የሚያደርጉትን የሰብዓዊ ድጋፍ ማሳደግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው በኢኳቶሪያል ጊኒ ማላቦ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው በ15ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሰብዓዊ ዕርዳታ እና ቃል ኪዳን ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በዚሁ መድረክ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ቀንድ በዓለም በአየር ንብረት ለውጥ እና በድርቅ ሳቢያ የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ከተከሰተባቸው ቀጠናዎች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለአፍሪካ የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያጠናክር ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም