ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ መንግስት ያዘጋጀላቸውን መኖሪያ ቤት ተረከቡ

132
አዲስ አበባ ጳጉሜ 4/2010 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፓትሪያክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ መንግስት ያዘጋጀላቸውን መኖሪያ ቤት ዛሬ ተረከቡ። ለብጹዕነታቸው የተዘጋጀው ቤት 2 ሺህ 200 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ግቢ ሲሆን መኖሪያ ቤቱ ለእንቅስቃሴያቸው እንዲመቻቸው ሆኖ ምድር ላይ ያረፈ ነው። የተዘጋጀውን መኖሪያ ቤት ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ያስረከቡት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ናቸው። የውጭና የአገር ውስጥ በሚል ተከፋፍሎ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶስ ወደ አንድነት መምጣታቸውን ተከትሎ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ኑሯቸውን ኢትዮጵያ ማድረጋቸው ይታወቃል። እስካሁን ድረስ ባለው ሂደትም በፓትሪያክ ጽህፈት ቤት ግቢ በተዘጋጀላቸው ጊዜያዊ መኖሪያ ቤት ቆይተዋል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም