የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ቤተ መንግስት የነበረው ህንፃ የምድር ቤት የፓን አፍሪካ ቋሚ ሙዚየም ሆነ

74

ግንቦት 17/2014/ኢዜአ/ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀዳማዊ ሃይለስላሴ ቤተ መንግስት የነበረው ህንፃ የምድር ቤቱ የፓን አፍሪካ ቋሚ ሙዚየም ሆነ።

በዩኒቨርስቲው ቅጥር ጊቢ የሚገኘው የግርማዊ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ቤተ መንግስት የሕንፃው የታችኛው ክፍል ወይም ምድር ቤት የፓን አፍሪካ ቋሚ ሙዚየም ሆኗል።

ሙዚየሙ  የተለያዩ  አገራት  አምባሳደሮች የዮኒቨርስቲው አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው  እንግዶች በተገኙበት  ተመርቋል።

የሙዚየሙ ዳይሬክተር ዶክተር ታከለ መርዕድ የፓን አፍሪካን እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ፎቶዎች እና የተለያዩ ስራዎች በቋሚነት የሚታይበት ሙዚየም ይሆናል ብለዋል።

የፓን አፍሪካ እንቅስቃሴ በአፍሪካዊያን መካከል የወንድማማችነት መሰረት የጣለ ልዩ አጋጣሚ በመሆኑ ለቀጣይነቱ መስራት ይገባል ብለዋል።

ለዚህ ደግሞ ዛሬ በሙዚየምነት የተሰየመው ታሪካዊ ህንፃ ትርጉም እንዳለው አስረድተዋል።

የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የተመሰረተበትን እለት ታሳቢ በማድረግ  የአፍሪካ አንድነት ቀን በየአመቱ በዛሬው ቀን ታስቦ ይውላል።