ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ከ20 እና ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ27 አትሌቶች ትወከላለች

82


ግንቦት 17 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ በታንዛንያ ዳሬ ሰላም በሚካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ከ20 እና ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ27 አትሌቶች ትወከላለች።


ሻምፒዮናው ግንቦት 19 እና 20 ቀን 2014 ዓ.ም ይካሄዳል።


27 አትሌቶችን ጨምሮ 32 አባላት ያሉት የሻምፒዮናው ልዑካን ቡድን ዛሬ ማለዳ ወደ ዳሬ ሰላም ማቅናቱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።


አትሌቶቹ በሁለቱም ጾታዎች ከ100 ሜትር እስከ 5 ሺህ ሜትር ባሉ ርቀቶችና የሜዳ ተግባራት በ20 የውድድር አይነቶች እንደሚሳተፉ ገልጿል።


ከ18 ዓመት በታች 15 እንዲሁም ከ20 ዓመት በታች 12 አትሌቶች ይሳተፋሉ።


በሻምፒዮናው ላይ ውጤታማ የሆኑ አትሌቶች ከሐምሌ 25 እስከ 30 ቀን 2014 ዓ.ም በኮሎምቢያ ካሊ በሚካሄደው የዓለም የ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና የመሳተፍ እድል እንደሚያገኙ ተነግሯል።


ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️