በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በበጋ የመስኖ ልማት ከ600 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በዘር ተሸፍኗል

172

ግንቦት 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በበጋ የመስኖ ልማት ከ600 ሺህ ሔክታር በላይ መሬት በዘር መሸፈኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።

የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴን፤ የተቋሙን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል።

በሪፖርታቸውም ባለፉት ዘጠኝ ወራት ምርታማነትን ለመጨመር በተለይም በበጋ የመስኖ ልማት የተከናወኑ ተግባራትን አብራርተዋል።

በሁለት ዙሮች በተከናወነው ልማት በመጀመሪያ ዙር ከ405 ሺህ እና በሁለተኛው ዙር ደግሞ ከ260 ሺህ በድምሩ 665 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል ብለዋል።

ከዚሁ የልማት ክንውን ከ23 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ ይገመታል።

በ2013/14 ምርት ዘመን ከ3 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች በኩታ ገጠም እርሻ የተሳተፉበት 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት መታረሱ ተገልጿል።

በግብርና ትራንስፎርሜሽን ክላስተር ደግሞ በ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር ማሳ ላይ ከ3 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮች እንዲሳተፉ መደረጉም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም