ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች አስመረቀ

231

ግንቦት 14 ቀን 2014 (ኢዜአ) ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 823 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ዶክተር ብርሃኑ አሰፋ እንደገለፁት ከተመራቂዎች መካከል 293ቱ ሴቶች ናቸው።

ዩንቨርሲቲው በአሸባሪው ህወሓት ከወደመ በኋላ በቅንጅት መልሶ ተቋቁሞ የመማር ማስተማር ስራውን ዳግም ጀምሮ ነው ዛሬ ለተማሪዎች ምርቃት የደረሰው ብለዋል፡፡

May be an image of 4 people, people standing and indoor

ለዛሬ ምርቃት የደረሱ ተማሪዎች የሽብር ቡድኑ በፈጸመው ወረራ ትምህርታቸው ቢስተጓጎልም ቅዳሜና እሁድ ጭምር አካክሰው ቆይታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ከተመረቁት ውስጥ 106ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆኑን ገልጸዋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም