ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ይገባል

456

ግንቦት 10 ቀን 2014 (ኢዜአ) ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የፍትህ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዴኦን ጢሞቴዎስ ተናገሩ።

ፍትህ ሚኒስቴር ከስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር በመሆን "የባለድርሻ አካላት የሙስና መከላከል ቅንጅት በኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ ምክክር እያካሄደ ይገኛል።

ውይይቱን አስመልክተው መልእክት ያስተላለፉት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዴኦን ሙስናና ብልሹ አሰራር የማህበረሰቡ አንገብጋቢ ችግር ሆኗል ብለዋል።

ሚኒስትሩ ሙስናና ብልሹ አሰራርን ለመቅረፍ በተናጥል የሚሰሩ ስራዎች ብቻ በቂ ባለመሆናቸው ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር የግድ ያስፈልጋል ብለዋል።

በውይይቱ የፌዴራል የስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የክልል የስራ ሀላፊዎችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።


የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም