በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ20ሺህ በላይ ሰዎች በቲቢ በሽታ ሕይወታቸው ያልፋል

221

ድሬዳዋ፤ ግንቦት 07 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ በየዓመቱ ከ20ሺህ በላይ ሰዎች በቲቢ(ሳምባ ምች) በሽታ ምክንያት ሕይወታቸው እንደሚያልፍ ተገለጸ።

በአለም ለ40ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ25ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘው የአለም የቲቢ ቀን በድሬዳዋም በከተማ ደረጃ ቀኑ እየታሰበ ነው።

በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ በአለም በበሽታው ከተጠቁ 30 ሀገራት አንዷ መሆኗ ተነግሯል።

በመድረኩ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰኢድ የበሽታው በትንፋሽ የሚተላለፍ መሆን ከአኗኗሯችን ሁኔታ ጋር ተዳምሮ የቁጥጥር ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል ብለዋል።

በድሬዳዋ አስተዳደር ከ2005 ዓ/ም ጀምሮ በ31 የህክምና መስጫ ማእከላት የቲቪ ህክምና አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ያሉት ሃላፊው፤ "አገልግሎቱን ካገኙት ተማሚዎች ውስጥ ሰባ ከመቶ ያህሉ ህክምናቸውን በስኬት ያጠናቀቁ ናቸው” ሲሉ አምልክተዋል።

በከተማ አስተዳደሩ የቲቢ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ተክሉ ሞሌ ባቀረቡት ጽሑፍ በኢትዮጵያ በአመት 20 ሺህ ሰዎች በቲቪ በሽታ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ገልጸዋል።

በዚህም ቲቢ በኢትጵያ በገዳይነቱ በአንደኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

አሁን እየተከበረ በሚገኘው የአለም የቲቪ ቀን ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃርና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የተገኙ ሲሆን በአስተዳደሩ ቲቪን ለመከላከል እየተሰሩ በሚገኙ ተግባራት ላይ ውይይት ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም