ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም ዓቀፍ የሞባይል አየር ሰዓት የመሙላት አገልግሎት ጀመረ

79
አዲስ አባባ ጳጉሜ 3/2010 ኢትዮ ቴሌኮም ዓለም ዓቀፍ የሞባይል አየር ሰዓት የመሙላት አገልግሎት መጀመሩን አስታወቀ። ቴሌኮሙ የጀመረው ኤሌክትሮኒክ የሞባይል አየር ሰዓት መሙያ አገልግሎት የቅድመ ክፍያና የጥምር ሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞችን ከውጭ አገር ወደ ሞባይል ቁጥሩቻቸው የአየር ሰዓት እንዲላክላቸው የሚያስችል ነው። ኢትዮ ቴሌኮም ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ፤ አገልግሎት ላይ የዋለው አዲሱ የኤሌክትሮኒክ አገልግሎት ከአሁን ጀምሮ ስራ ላይ የሚውል ሲሆን በወጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ለሚኖሩ ዘመድ ወዳጆቻቸው የአየር ሰዓቱን በመግዛት ለመላክ ያስችላል። አገልግሎቱ በመላው አለም ተደራሽነት ባላቸው አገሮች የበዓል ቀናትን ጨምሮ 24 ሰዓት የሚሰጥ ስለሆነ ከ25 ብር ጀምሮ በመግዛት ወደ አገር ቤት ስልክ ተጠቃሚዎች መላክ ያስችላቸዋል፡፡ የቴሌኮሙ ደንበኞች www.Senditoo.com ወይም  www.worldremit.com ላይ በመግባት መግዛትና መላክ  እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ የሞሉትና የላኩት መጠንና የአየር ሰዓቱ የሚያበቃበት ቀን መረጃ በ994 እንዲደርስ ይደረጋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም