የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ምርጫ እንዲካሄድ ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየት ጀመረ አሶሳ

159

ግንቦት 04 ቀን 2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ምርጫ ማካሄድ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአሶሳ ከተማ መወያየት ጀመረ፡፡

በቦርዱ የምርጫ ኦፕሬሽን ምክትል ማናጀር አቶ ብሩክ ወንድወሰን በወቅቱ እንዳስታወሱት፤ ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በክልሉ አንዳንድ የምርጫ ክልሎች አልተካሄደም።

በመሆኑም ምርጫ ባልተካሄደባቸው የምርጫ ክልሎች ምርጫ ለማካሄድ ቦርዱ በክልሉ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላትን ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ማወያየቱን ጠቅሰዋል፡፡

ቦርዱ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ካደረገ በኋላ ምርጫው እንዲካሄድ ለማድረግ ማቀዱን የጠቆሙት አቶ ብሩክ፤ በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ሁኔታ ዳሰሳ ጥናት ሰነድ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የዚህ ውይይት ዓላማ በሰነዱ ላይ ግብዓት በማሰባሰብ ለቀጥይ ስራ ምቹ ሁኔታ መፍጠር መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ የብልጽግና፣ እናት፣ አብን፣ ኢዜማ እና ሌሎችም ፓርቲዎች ተወካዮች፣ የሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሉ ፖሊስ፣ ሠላም ግንባታ ጸጥታ ቢሮ እና የቦርዱ አመራሮች እየተሳተፉ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም