ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ
164
ግንቦት 02 ቀን 2014 (ኢዜአ) ኢትየጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸው ተገለጸ።
ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት በባዮ ቴክኖሎጂ፣ በህዋ ሳይንስ እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል፡፡
እስከ 2025 በሚቆየው ይህ የትብብር ስምምነት የሰው ሃይል ስልጠና፣ የባለሙያ ልውውጥ፣ በኢኖቬሽን ሰታርትአፕ እና በሌሎች የሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡
መሰከረም ወር ላይ የተቋቋመው የሁለቱ ሀገራት የቴክኒክ ኮሚቴ ያዘጋጀውን የትብብሩን ዝርዝር ተግባራት ሰምምነት በኢትየጵያ በኩል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ እና በደቡብ አፍሪካ በኩል ደግሞ የሳይንስና ኢኖቬሽን ዲፓርትመንት ተወካይ ሚስተር ዳን ዱ ቶይት ፈርመወታል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ በህዋ ሳይንስ፣ በምርምር እና በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፍ ደቡብ አፍሪካ ያላትን የተሻለ ልምድ ኢትዮጵያ ትወስዳለች ብለዋል፡፡
ሁለቱ ሀገራት በሳይንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ከዚህ በፊት መፈራረማቸው ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡