የሶማሌ ክልል የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ221 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የሶማሌ ክልል የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ221 ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ
126
ሚያዚያ 26 ቀን 2014 (ኢዜአ) የሶማሌ ክልል የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአምስት ሴቶች እና ለ216 ወንዶች በድምሩ ለ221 ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን የክልሉ የይቅርታ ቦርድ ገለጸ።
የቦርዱ ሰብሳቢና የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አህመድ ሐጂ ሰመተር ዛሬ እንደገለጹት፤ በይቅርታ ከእስር የተለቀቁት የይቅርታ መስፈርቱን አሟልተው የተገኙ ናቸው።
ከእስር የተፈቱ የህግ ታራሚዎች ከስድስት ወር እስከ አምስት አመት ተፈርዶባቸው የነበሩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
ታራሚዎቹ የይቅርታ ቦርድ ወሳኔ ያገኙት በማረሚያ ቤት ቆይታቸው መልካም ስነ ምግባር ያሳዩ፣ የእስር ጊዜያቸውን አንድ ሦስተኛ ያጠናቀቁና ለቦርዱ ይቅርታ እንዲደረግላቸው ያመልከቱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በአስገድዶ መድፈር፣ በሰው ህይወት ማጥፋት፣ በሙስና እንዲሁም ለህብረተሰቡ ሰላምና ደህንነት አደጋ ሊያስከትሉ በሚችሉ ወንጀሎች ተከሰው የተፈረደባቸው በይቅርታው ውስጥ አለመካተታቸውን ተናግረዋል።
በሶማሌ ክልል የይቅርታ ቦርድ ከተካተቱት ተቋማት መካከል የክልሉ ፍትህ ቢሮ፣ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን፣ ፀጥታ ዘርፍ ቢሮ፣ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ ጤና ቢሮ፣ ፓሊስ ኮሚሽን ይገኝበታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ