እስልምና መነሻው ሰላም፣ መዳረሻውም ሰላማዊነት ነው – አቶ መለሰ ዓለሙ

107

ሚያዚያ 24 ቀን 2014 (ኢዜአ) እስልምና መነሻው ሰላም፣ መዳረሻውም ሰላማዊነት ነው ሲሉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ አቶ መለሰ ዓለሙ ገለጹ።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ታላቁ የኢድ ሶላት ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ መለሰ ዓለሙ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ብለዋል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በረመዳን ወር ያሳየውን መልካም ተግባራት በሌሎች ቀናትም ተግባራዊ ሊያደርገው እንደሚገባም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በሁሉም የሃይማኖት ተከታዮች በጋራ የተገነባች አገር ናት ያሉት አቶ መለሰ፣ የቀደመውን ሰላም እና አንድነት አስቦ በሰላም መኖር ይገባልም ብለዋል።

ኢትዮጵያን በጋራ ተባብረን እንደገነባናት ሁሉ አሁንም በጋራ ልናሻግራት ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት የሚንቀሳቀሱ አካላትንም በጋራ ልንመክታቸው ይገባል ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ጠላትን የምናሸንፈው በአንድነት በመሆኑ አንድነታችንን ልናስጠበቅ ይገባል በማለት ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም