ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ጾም ያሳየውን መተጋገዝ አጠናክሮ ሊያስቀጥል ይገባል -አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ

138

ጅግጅጋ ሚያዚያ 23/2014 (ኢዜአ) ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ያሳየውን መተጋገዝ ወደፊትም አጠናክሮ ሊያስቀጥል እንደሚገባ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ አስገነዘቡ።
ርእሰ መስተዳድሩ ለመላው እስልምና ሀይማኖት ተከታዮች ለ1443ኛ የኢድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

ርእሰ መስተዳደሩ አቶ ሙስጠፌ ሙሀመድ በመልካም ምኞት መግለጫቸው ባስተላለፉት መልእክት ህዝበ ሙስሊሙ በረመዳን ወር ያሳየውን በተጋገዝና መረዳዳት ወደፊትም በማንኛውም ወቅት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ።

“በክልሉ በረመዳን ወር በተለይም በአብዛኛው ወጣቶችና ሴቶች ዘንድ በራሳቸው ተነሳሽነት ያሳዮት የመረዳዳት ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል” ብለዋል።

ህዝበ ሙስሊሙ የኢድ አል ፈጥር በዓልን እርስ በእርሱ በመረዳዳትና ያለው ለሌለው  በማካፈል ሊያከብር እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

ርእሰ መስተዳደሩ ለሀይማኖቱ ተከታዮች እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በዓሉ የፍቅርና የስኬት እንዲሆን ተመኝተዋል።