የፍቼ ጨምባላላ ማህበራዊ ዕሴቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል -ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ

78

ሀዋሳ ሚያዚያ 20/ 2014 (ኢዜአ) የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በአል የሆነውን የፍቼ ጨምባላላ ማህበራዊ እሴቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ አስገነዘቡ ።

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በፊቼ የሲፓዚየም መክፈቻ ላይ እንደገለጹት የፊቼ ጫምባላላ በዓል ሲዳማ ክልል ሆኖ ከተደራጀ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋራ መከበሩ ልዩ ያደርገዋል።


ባለፉት ሁለት ዓመታት በኮቪድ 19 ምክንያት ሳይከበር ቢቆይም ዘንድሮ በአደባባይ በጋራ ማክበር መቻሉን ጠቁመዋል።

የሲዳማ ህዝብ ክልል ሆኖ ለመደራጀት ቀደም ባሉት ዓመታት በጋራ ያደረገውን የተጠናከረ ትግል በልማቱ ለመድገም አንድነቱን የበለጠ ማጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል።


የሲዳማ ብሄር የዘመን መለወጫ በዓል የሆነው ፊቼ ጨምበላላ ያሉትን የመረዳዳት፣ የመተጋገዝና የአብሮነት እሴትን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አስገንዝበዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም