አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ሥራዎችን በአራት ምዕራፎች ከፋፍሎ እያከናወነ ነው

101

ሚያዚያ 18 /2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሥራዎችን በአራት ምዕራፎች ከፋፍሎ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ።

ኮሚሽኑ እስካሁን ያከናወናቸውን በቀጣይ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ለምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች እያቀረበ ይገኛል።

የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ኮሚሽኑ እስካሁን የሠራቸውን ተግባራትና  በቀጣይ ስለሚያከናውናቸው ተግባራት ሪፖርት አቅርበዋል።

በዚህም አገራዊ ምክክሩ በአራት ምዕራፎች ተከፋፍሎ ሥራውን መጀመሩን ነው የገለጹት።

እነዚህም የቅድመ ዝግጅት፣ የዝግጅት፣ የምክክርና ክንውን ሂደትና የምክክር ውጤቶች መተግበሪያ ምዕራፎች መሆናቸውን ዘርዝረዋል።

በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ የተከናወኑትንና ወደ ፊትም የሚሰሩትን ሥራዎች ፕሮፌሰር መስፍን አስረድተዋል።

በቀረቡት ሪፖርቶች ላይ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎችና ከፍተኛ አመራሮች አስተያየትና ቀጣይ አቅጣጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም