ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ 74 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ወደ መቀሌ እቀኑ

437

ሚያዚያ 15 ቀን 2014 (ኢዜአ) ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ 74 ከባድ ተሽከርካሪዎች ከሰመራ ተነስተው ወደ ትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ማምራታችውን የአደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

ኮሚሽኑ ለኢዜአ እንዳስታወቀው፤ ነዳጅን ጨምሮ የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎችን የጫኑ 74 ከባድ ተሽከርካሪዎች ዛሬ 10 ሰዓት ገደማ ወደ ትግራይ ተንቀሳቅሰዋል።

ከከባድ ተሽከርካሪዎቹ መካከል 42ቱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሲሆኑ 1 ሺህ 456 ነጥብ 7 ሜትሪክ ቶን ድጋፍ የጫኑ መሆናቸው ተገልጿል።13ቱ ደግሞ የካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስ መሆናቸው ።ስድስት ከባድ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ነዳጅ የጫኑ እንደሆኑም ታውቋል።

በተለያዩ ጊዜያት ወደ ትግራይ ክልል የተለያዩ ቁሳቁሶችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች እየገቡ ሲሆን ወደ ክልሉ ከሄዱ ከባድ ተሽከርካሪዎች መካከል 1 ሺህ 25 የሚሆኑት እንዳልተመለሱ የኮሚሽኑ መረጃ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም