ለተፈናቀሉ ወገኖች ለትንሳዔ በዓል መዋያ ከ450 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ ተደረገ

263

ጂንካ ፣ሚያዚያ 14/2014 (ኢዜአ) የሃይማኖት ተቋማት በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካና አከባቢዋ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ወገኖች ለትንሳዔ በዓል መዋያ ከ450 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ አደረጉ።

ድጋፉንካደረጉትመካከልየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት  ተወካይ ቀሲስ  መላከ ፀሀይ ጥላሁን፤ ሀገረ ስብከቱ ቀደም ሲልም ለተፈናቀሉ ወገኖች 50 ኩንታል የጤፍና የበቆሎ ዱቄት  ማበርከቱን አስታውሰዋል።

ዛሬደግሞ ከ200 ሺህ ብር በላይ የሚገመት 48 ኩንታል ዱቄት፣የምግብ ዘይት እና አልባሳት ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል።

ወቅቱ በክርስትናም ሆነ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የፆም ወቅት በመሆኑ በጋራ የምንቆምበትና ተጋግዘን ችግርን የምናልፍበት  ወቅት ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስትያን የሶዶ ሀገረ ስብከት፣ የጂንካ፣ የሐመርና የኦሞራቴ ካቶሊክ ቤተክርስትያናት በደቡብ ኦሞ ዞን  ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች  ለበዓል መዋያ የሚሆን የ251 ሺህ ብር  የሚገመት ድጋፍ አድርጋለች።

ከድጋፉ መካከል ለትንሳዔበዓልየሚሆኑ ሁለት ሰንጋ በሬ፣ የምግብ ማብሰያ ቁሳቁስና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ይገኝበታል።

አባ ማይክል ካሳዬ ከሐመር ወረዳ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ፣ አባ ደምሴ ጉራሮ ከጂንካ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያንና አባ ዋዶ ክንፌ ከኦሞራቴ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን የተፈናቀሉ ወገኖችን በመጠየቅ ድጋፉን አበርክተዋል።

የደቡብኦሞዞኑ አደጋ ስጋት አመራር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዱባ ያራ  ፤የሃይማኖት ተቋማቱ በስፍራው በመገኘት ተጎጂዎችን በማበረታታት ላደረጉት ድጋፍ አመስግነዋል ።

ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረትም የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ ሌሎችም ግብረሰናይ ድርጅቶችና በጎ  አድራጊ  ግለሰቦች የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

ድጋፍ ከተደረገላቸው የሜፀር ከተማ ነዋሪወይዘሮ እቴቱ አበበ ፤ እየተደረገላቸው ላለው ድጋፍ አመስግነው በዘላቂነት ለመቋቋም የመንግስትን  ድጋፍ እንደሚሹ   ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም