የስቅለት በዓል በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ተከብሯል

419

ሚያዚያ 14/2014/ኢዜአ/ የስቅለት በዓል በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስት ማርያም ገዳም በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ተከብሯል፡፡

በዓሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ የእምነቱ አባቶችና ምእመናን በተገኙበት በስግደትና በጸሎት ተከብሯል።

ዕለቱን የሚያስቡ መንፈሳዊ ትምህርቶችና መዝሙሮችም ቀርበዋል፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን የተቀበላቸው መከራዎችም በመርሃ ግብሩ ላይ ተዘክረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም