ምሁራን ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል

488

ደብረብርሃን ሚያዚያ 9/2014 (ኢዜአ) ምሁራን ያላቸውን እውቀትና ክህሎት ተጠቅመው የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ሰላም ሚኒስቴር አስገነዘበ።

ሚኒስቴርመስሪያቤቱበምስራቅ አማራ ከሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች ጋር በብሄራዊ ምክክሩ ላይ ያተኮረ ውይይት በደብረብርሃን ከተማ አካሂዷል።

ከደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ጋር በመቀናጀት በተዘጋጀው ውይይት ላይ የሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ   እንዳሉት የሀገሪቱን ዘላቂ ሰላምና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያስችል አካታች ምክክር በሀገር ደረጃ ይካሄዳል።

"መድረኩየታለመለትን ግብ እንዲመታ ፖለቲከኞች፣ ልሂቃንና ማህበረሰቡ ከስሜት በጸዳ መልኩ  ተሳትፎ በማድረግና በመደማመጥየታለመትን ሀገራዊ ግብ ማሳካት ያስፈልጋል" ብለዋል።

"በምክከሩ የሠላም ግንባታና የአብሮነት እሴቶችን በግብዓትነት በመጠቀም ከራስ አልፎ የሌሎችን ችግር  መመልከት ተገቢነት አለው" ሲሉም አክለዋል ፡፡

የአገር ጉዳይ ያገባኛል የሚል አካል ሁሉ በመቻቻልና በምክንያታዊነት ላይ የተመሰረተ ውይይት እንዲያካሂድ ምሁራን ግንዛቤ በመፍጠር ርገድ የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

በደብረብረሃንዩኒቨርስቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚደንት ዶክተር ደረጀ አንዳርጌ በበኩላችው "አሁን ላይ ሰላም ለኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ምክክሩ በሀቅና በትብብር መንፈስ መካሄድ አለበት" ብለዋል።

የሀገር በቀል የግጭት አፈታትና የእርቅ ስርዓታችንን በመመርመር ለብሄራዊ ምክክሩ መጠቀም እንደሚገባ ጠቁመው ለምክክሩ ስኬት ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አመልክተዋል።

"ምክክሩበሚያግባቡን ላይ ተግባብተን፣ በልዩነታችን ደግሞ ተከባብረንና ተቻችለን ለመኖር የሚያስችል መደላድል ለመፍጠር ይረዳል" ሲሉ ጠቅሰዋል።

"በሀገራችን ዘመን ተሻጋሪ የነበረው የአብሮነትና የሰላም አሴት በሃሰት ትርክት እየተሸረሸረ መጥቷል" ያሉት ዶክተር ደረጀ ወጣቱን ትውልድ በስነ ምግባር ማነጽ የወቅቱ ጥያቄ መሆኑን አመልክተዋል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፈሰር አበባው አያሌው  ባቀረቡት ጥናታዊ ጹሁፍ  "አካታች የምክክር መድረኩ በህዝቦች መካከል ለዘመናት የቆየን ሰላምና አንድነት በማጽናት አገርን  ከመፍረስ ይታደጋል" ብለዋል፡፡

ምሁራንበሚያካሂዱት ሳይንሳዊ ምርምር የዓለምን ተሞክሮ በማምጣትና ህብረተሰቡን በማንቃት ለምክክሩ ስኬት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አስገንዝበዋል።

በውይይት መድረኩ ላይ በምስራቅ አማራ የሚገኙት የወልዲያ፣ ወሎ፣ መቅደላ አምባና የደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ   ተወካዮች  ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም