ከጋምቤላ ከ966 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ተላከ

357

ጋምቤላ ፤ ሚያዚያ 9/2014 (ኢዜአ) በጋምቤላ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ966 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መላኩን የክልሉ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ አኳታ ቻም ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ለብሔራዊ ባንክ የተላከው ወርቅ በክልሉ ዲማ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላ እና መንጌሽ ወረዳዎች ባሉ ባህላዊ ወርቅ አውጪዎች የተመረተ ነው።

ባለፈው 9 ወራት ከክልሉ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ የተደረገው የወርቅ መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ብልጫ እንዳለው ተናግረው ምርቱ በኮንትሮባንድ ንግድ እንዳይባክን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት ዘንድሮ ካለፈው ዓመት የተሻለ የወርቅ ምርት ለብሔራዊ ባንክ መላኩን አስረድተዋል።

May be an image of 7 people, body of water and tree

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለብሔራዊ ባንክ ከተላከው የወርቅ ምርት ከ49 ሚሊዮን 870 ሺህ በላይ ዶላር የውጪ ምንዛሬየሚያስገኝ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል።

በቀጣይም የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል የሚደረገውን ቁጥጥር በማጠናከር በበጀት ዓመቱ 1ሺህ 600 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ገቢ ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም