የኮምዩኒቲው አባላት ለትምህርት ተቋማት መልሶ ግንባታ የሚውል የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ

108

ሚያዝያ 01 ቀን 2014 (ኢዜአ) በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት ለትምህርት ተቋማት መልሶ ግንባታ የሚውል የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

የኮምዩኒቲው አባላት ለተለያዩ አገራዊ ጥሪዎች የሚያደርጉትን ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኃይል በአሸባሪው የሕወሓት ቡድን የወደሙና የፈራረሱ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በአገሪቷ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ያሰባሰበውን ሃያ ሺህ የአሜሪካ ዶላር (አንድ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር) ማሰባሰቡን ኢዜአ ካምፓላ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ግብረ ኃይሉ በአገር ቤት በትምህርት ሚኒስቴር ለዚሁ ድጋፍ በተከፈተው የሒሳብ ቁጥር በማስገባት የገቢ ደረሰኙን በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለምፀሐይ መሰረት ትናንት በኤምባሲው በመገኘት አስረክቧል።

በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ አምሃ ይርጋ በትምህርት ተቋማት መልሶ ግንባታ ድጋፍ በማድረግ የችግሩ ተጠቂ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኃይሉ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አብዲ አደን በበኩላቸው የኮምዩኒቲው አባላት ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር እንድትሻገር በጋራ በመቆም ድጋፋችንን ማድረግ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለምፀሐይ መሰረት በኡጋንዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም በተለያዩ አገራዊ ጥሪዎች ላይ ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

የኮምዩኒቲው አባላት ይህን ተምሳሌታዊ ድርጊት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኃይል አባላት በኡጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለምፀሐይ መሰረት ጋር በአገራዊ ጉዳዮችና በቀጣይ በሚሰሯቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ምክክር ማድረጋቸው ተገልጿል።

በኡጋንዳ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት ከዚህ ቀደም ለአገር መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ካምፓላ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከቀናት በፊት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋማቸውን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት በጦርነትና ግጭት ሳቢያ በጠቅላላ 1 ሺህ 393 ትምህርት ቤቶች መውደማቸውን ገልጸዋል።

የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት 50 ቢሊዮን ብር

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም