ኢንስቲትዩቱ ያለማቸውን አራት ቴክኖሎጂዎች ይፋ አደረገ

106

መጋቢት 29/2014 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያለማቸውን አራት ቴክኖሎጂዎች ይፋ አደረገ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ያለማቸውን ቴክኖሎጂዎች 3ዲ ፕሪንተር ፤ፐላንት ዌት ወይም (መሬት ላይ ሆኖ በየትኛውም የህዋ አካል ላይ ክብደትን ለማወቅ የሚያስችል ቴክኖሎጂ) ባለ 70 ሚሊሜትር ሪፍራክተር ቴሌስኮፕ እና  ባለ 200 ሚሊ ሜትር ቴሌስኮፕ ናቸው፡፡

የኢንስቲቱዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ፤ የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ባለስልጣን ኢንስቲትዩቱ ላለማቸው ቴክኖሎጂዎች የባለቤትነት እውቅና መሰጠቱን ተናግረዋል ፡፡

የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳሮች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲዎችና ተቋማት ባለሙያዎች ቴክኖሎጂዎችን ለማበልጸግ የሚያስችላቸውን ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉንም እንዲሁ፡፡

ስልጠናውን ከወሰዱት መካከል ከሲዳማ ክልል የመጡት ወይዘሮ ቤተልሔም ዳንኤል እንዳሉት፤ በስልጠናው ያገኙትን እውቀት በክልሉ ለሚገኙ ተማሪዎች በማካፈል ተግባራዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰሩ አስረድተዋል፡፡

ከድሬደዋ ከተማ መስተዳደር የመጡት አቶ ኢማም አብዱልቃድር በበኩላቸው፤ ከኢንስቲትዩቱ ያገኙትን ልምድ በክልላቸው ለሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እንደሚያካፍሉ ገልጸዋል፡፡

በተለይ የ "3ዲ" ቴክኖሎጂ አሁን ላይ ኦርጋኖችን ፕሪንት የማድረግ ደረጃ ላይ መድረሱንም ተናግሯል፡፡

እንደ ሀገር ትልቅ ደረጃ ለመድረስ የያዝነው ውጥን የሚሳካው ወጣቶችን በቴክኖሎጂ ማነጽ ስንችል ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም በኢንስቲትዩቱ የበለጸጉትን አይነት የቴክኖሎጂ ውጤቶች በስፋት በማቅረብ ወጣቶችን  ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም